የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድጋፉን ከባንኩ የስራ ሃላፊዎች እጅ የተቀበሉ ሲሆን ባንኩ ላደረገው አስተዋጽኦም በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ምስጋናን ችረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ የለገሰውን ጨምሮ ከአጠቃላይ የባንክ ዘርፍ በድምሩ ለ“ገበታ ለአገር “ፕሮጀክት እስካሁን 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መገኘቱ ተመልክቷል።