የኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ታህሳስ 3 ይጀምራል

የኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ ይፋ አድርጓል።

የፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒው በኮቪድ ውስጥ ሆኖ የኢትጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ለማስጀር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑንም አስታውቋል።

በዚህም ዝግጅቱን መሠረት በማድረግ የፕሪሚየር ሊግ ውድድሩ ታህሳስ 03 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር ለተሳታፊ ክለቦች ማሳወቁን ከኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።