የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት ወር እንደሚሰጥ ተገለጸ።

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት ወር እንደሚሰጥ ገለጸ። ኤጀንሲው እንዳስታወውም በዚህ አመት የትምህርት ዘመን የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ሳይጨምር 620 ሺህ ተማሪዎች ተመዝግበው ፈተናውን በመጠባበቅ ላይ እነደሚገኙ የኤጀንሲው አስታውቃል። በተጨማሪም በማንኛውም ሰዓት ፈተናውን መስጠት የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን እና በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች የኢኮኖሚክስ ትምህርት ባለመሰጠቱ ፈተናው የማይሰጥ መሆኑንም አያይዘው ገልጸዋል።ምንጭ ፦ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ

#አዲስ_ነገር