NewsOthers

የጎርፍ አደጋ በአፍሪካ ቀንድ

ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ በ1ወር ጊዜ ውስጥ አንድ መቶ ሰዎች በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ማለፉንና ከሟቾቹ መካከል 16 ያህሉ ህጻናት መሆናቸውን ያሁ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ከሟቾቹ መካከል 46ቱ ከኬንያ፣ 33 ቱ ከኢትዮጵያ እንዲሁም 32ቱ የሶማሌ ዜግነት ያላቸው መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በሶስቱ ሀገራት የጎርፍ አደጋው 700 ሺህ ያክል ሰዎችን ከቤት ንብረታቸው ማፈናቀሉን እንዲሁም የእርሻ መሬቶች ጭምር በውሃ መጥለቅለቃቸው በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

ቀጠናው በተለያየ ጊዜ ለሚከሰት የአየር ንብረት ለውጥ አደጋ ተጋላጭ እንደሆነና ካለፉት 40 ዓመታት ወዲህ የከፋ ነው በተባለው አስከፊ ድርቅ ሳቢያም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዎሪዎች ለችግር መጋለጣቸው ተጠቁሟል፡፡