የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር የወጣው አዋጅ በፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደሚወሰን ተነገረ።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ የጸደቀውና የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር የወጣው አዋጅ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ብሄር በሄረሰቦችና ሕዝቦች ማንነታቸውና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚኖራቸው የመቀመጫ ወንበር ብዛት በፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደሚወሰን ተነገረ። የተለያዩ ማሻሻያዎች የተደረጉ ሲሆን ከዚህም መሃል በክልልና በፌዴራል መንግስት መካከል አለመግባባቶች ሲከሰቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሁለቱም ወገን ጥያቄ ሳይቀርብለት ችግሩ እየተባባሰ መሆኑን ካመነበት ጣልቃ መግባት እንደሚችልም ተነግራል።

ምንጭ፦ ኢቢኤስ አዲስ ነገር