ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን በትግራይ ውስን ቦታዎች እንቅስቃሴዎቼን አቁሚያለሁ አለ፡፡

ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን የተባለው ግብረሰናይ ድርጅት በ3 ባልደረቦቹ ላይ በተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ እስኪጣራ ድረስ በትግራይ ውስን ቦታዎች የሰብዓዊ ድጋፍ እንቅስቃሴዎቼን አቁሚያለሁ አለ፡፡ እንቅስቃሴ የቆሙባቸው አካባቢዎች በማዕከላዊና ምስራቃዊ ትግራይ የሚገኙት አቢይ አዲ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት ሲሆኑ ነገር ግን በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ሰባአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚሰጠውን እገዛ በጥንቃቄ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። በተጨማሪም የቡድን አባላቱ ግድያ ላይ አስቸካይ የማጣራት ስራ እንዲሰራ ጠይቆ ለሰራተኞቼ ደህንነት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ሲሉ ጥሪ አቅርብዋል።

ምንጭ፦ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን (MSF)