ፌስቡክ መቀመጫቸውን ግብጽ ያደረጉና ኢትዮጵያ ሱዳንና ቱርክ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው ያላቸውን 17 አካውንቶችን ማጥፋቱን አስታውቋል፡፡

#ፌስቡክ መቀመጫቸውን ግብጽ ያደረጉና ኢትዮጵያ ሱዳንና ቱርክ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው ያላቸውን 17 አካውንቶችን ማጥፋቱን አስታውቋል፡፡ኩባንያው ይህን የገለጸው በድረገጹ ላይ ይፋ ባደረገው የተቀናጁ ሃሰተኛ ባህሪያት በሚል ያደረገውን ምርመራና የወሰዳቸውን እርምጃዎች ባስታወቀበት ሪፖርቱ ላይ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ከ1 ሺ በላይ የፌስቡክ አካውንቶች፣ 290 የኢንስታግራም አካውንቶች፣ 255 ገጾችና 35 የፌስቡክ ግሩፖችን አጥፍቻለው ብሏል፡፡ከነዚህ መሃል ታዲያ 17 የፌስቡክ አካውንቶች፣ ስድስት ገጾችና ሦስት የኢንስታግራም አካውንቶች መቀመጫቸው ግብጽ ሆኖ ለኢትዮጵያ ለሱዳንና ለቱርክ ህዝቦች የተሳሳቱና ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ሃሰተኛ መልዕክቶችን መለጠፋቸውን ተከታትሎ በመድረሱ ማጥፋቱን አስታውቋል፡፡እነዚህ አካውንቶችና ገጾች በአገራችን ሲሰራጩ የነበረው የአማርኛ ቋንቋን በመጠቀምና ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖሩ እንዳለ በማስመሰል ሲሆን ስለ ግብጽ እንዲሁም ስለ ሱዳንና እስራኤል ግንኙነት በጎ በጎውን እያወሩ ስለ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ደግሞ አሉታዊ መረጃን ሲያሰራጩ ነበር ብሏል ፌስቡክ በሪፖርቱ፡፡

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs