News

አዲስ ነገር – ስለኢትዮጵያ የፎቶግራፍ አውደርዕይ በጎንደር ከተማ

ስለኢትዮጵያ የተሰኘው 12ኛው ዙር የፎቶግራፍ አውደርዕይ በጎንደር ከተማ ተካሄዷል ስለኢትዮጵያ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን ዛሬ በጎንደር ከተማ የተጀመረ ሲሆን በመክፈቻው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የጎንደር ከተማ ባለስልጣናት፣ ታዋቂ ሰዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን ከፎቶግራፍ ኤግዚቢሽኑ ጎን ለጎንም የመገናኛ ብዙሃንን ሚና የሚያነሱ ሦስት የጥናት ጽሑፎች ቀርበዋል። ለሁለት ቀን በሚቆየው በዚህ ኣውደርዕይ ላይ ሚዲያና ብሔራዊ ጥቅም፣ ሚዲያና ሀገራዊ ኃላፊነትና ሚዲያ ከአዲሱ የማህበራዊ ሚዲያ አንፃር በሚሉት ጥናታዊ ጽሑፎች ላይ ውይይት ተካሄዷል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New