አዲስ ነገር – አሜሪካ ዳግም ስለተቀሰቀሰው ጦርነት
ዳግም መቀስቀሱ የተነገረው ጦርነት ለሰብአዊ ድጋፍ እንዲሁም ለዘላቂ ሰላም የሚደረጉ ጥረቶችን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ስትል በውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ በኩል ስጋትዋን ገልጻለች፡፡የኢትዮጵያ መንግስትና የህወሃት ቡድን የሰላም ጥረታቸውን እንዲያጠናክሩ ጥረት ስታደርግ መቆየቷን ያስታወሰችው አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት ላለፉት 5 ወራት ለሰብዓዊ እርዳታ ፍሰት ሲል የተኩስ አቁም ማወጁ እንዲሁም ዘላቂ የተኩስ አቁም እንዲኖር በህወሃት በኩል መጠየቁ በጎ ጅምሮች እንደነበሩ በመግለጫዋ ጠቅሳለች፡፡ሁለቱም አካላት ላለፉት 5 ወራት ግጭትን በመቀነስ የሰብአዊ ድጋፍ ፍሰት እንዲሰምር የበኩላቸውን ጥረት ማድረጋቸው የብዙ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ የቻለ ነበር ያለችው አሜሪካ አሁን ላይ የሚሰሙ የጦር ሜዳ ተኩስ ልውውጦች ቀርተው ዘላቂ የተኩስ አቁም አለመካሄዱ እየታዩ የነበሩ በጎ ሂደቶችን የሚጎዳ ነውም ብላለች፡፡የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም ንግግር የሚያደርግ ኮሚቴ ማቋቋሙንና ለሰላማዊ ንግግር ዝግጁ መሆኑን እንደምትገነዘብ የገለፀችው አሜሪካ አሁን ላይ ሁሉም አካላት እንደ ምግብና ነዳጅ ያሉ የሰብአዊ ድጋፎች እንዳይስተጓጎሉ እንዲያግዙና የሰብአዊ ድጋፉን ለወታደራዊ አላማ ከመጠቀም እንዲቆጠቡም አሳስባለች፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New