አዲስ ነገር – አጫጭር የዓለም መረጃዎች
7 አገራትየበለፀጉት የቡድን 7 አገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች በሩሲያ የነዳጅ ምርቶች ላይ በሚጣል አዲስ የዋጋ ገደብ ዙሪያ ሊመክሩ መሆኑ ተሰምቷል ::የአሜሪካው የብሔራዊ ደህንነት ም/ቤት ቃለ አቀባይ ጆን ኪርቢ በሩሲያ የወጪ የነዳጅ ምርቶች ላይ የዋጋ ገደብ ለመጣል የቡድን 7 አገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች ዛሬ ይመክራሉ ብለዋል።በሩሲያ የነዳጅ ምርቶች ላይ የሚጣለው የዋጋ ገደብ አገሪቱ ከነዳጅ የምታገኘውን ገቢ ለመቀነስ ያለመ ነው ሲሉ ጆን ኪርቢ መናገራቸውን አናዶሉ ዘግቧል።
ግዙፉ የጀርመን አየር መንገድ ሉፍታንሳ 8 መቶ ያክል በረራዎቹን አቋረጠ ።ሉፍታንሳ አየር መንገድ በዛሬው እለት 8 መቶ ገደማ በረራዎቹን ያቋረጠው የአየር መንገዱ በርካታ አብራሪዎች አድማ በመምታታቸው መሆኑ ነው የተነገረው።አየር መንገዱ በጀርመን የበርሊን እና ሙኒክ ከተሞች የሚያደርገውን በረራዎች በማቋረጡ ከ 1 መቶ 30ሺ በላይ ተሳፋሪዎች መስተጓጐላቸውን ቲአርቲ ወርልድ ዘግቧል።
ሪፐብሊክ ኮንጎ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጐ በተከሰተው የኮሌራ በሽታ 48 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል።በአገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል የሳንሱሪ ግዛት በተከሰተው የኮሌራ በሽታ ከሞቱት 48 ሰዎች ባሻገር 3 መቶ 8 ዜጎች በበሽታው መያዛቸው ነው የተገለፀው።የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ከለጋሽ አገራት ጋር በመሆን ለተጎጂዎች ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ አናዶሉ ዘግቧል።
በቻይና ባገረሸው የኮሮና ወረርሽኝ በ21 ሚሊየን ሰዎች ላይ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።የቻይና ባለስልጣናት ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደቡን የጣሉት የ21 ሚሊየን ሰዎች መኖሪያ በሆነቸው የቼንግዱ ከተማ መሆኑ ነው የተሰማው።በከተማዋ በተጣለው ጥብቅ ገደብ በርካታ ሆስፒታሎች እና የገበያ ማዕከላት ሁሉ ተዘግተዋል ሲል ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል።
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New