News

አዲስ ነገር – አጫጭር የዓለም መረጃዎች

#ብሪታንያ

ሊዝ ትረስ አዲሷ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ።ከቀድሞው የብሪታንያ የገንዘብ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ጋር ለወራት ብርቱ ፉክክር ሲያደርጉ የቆዩት ሊዝ ትረስ የቀድሞውን የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን በመተካት አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመርጠዋል።የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሊዝ ትረስ የወግ አጥባቂ የኮንዘርቫቲቭ ፓርቲ ሊቀመንበርም ሆነው መመረጣቸውን አርቲ ዘግቧል።

#ኬንያ

የኬንያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የዊልያም ሩቶ አሸናፊነትን በይፋ አረጋግጧል።በፕሬዚዳንታዊ ተቀናቃኙ ራይላ ኦዲንጋ የቀረቡት የምርጫ መጭበርበር ክሶች አንዳቸውም ተቀባይነት እንደሌላቸው በመግለፅ ነው የኬንያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የዊልያም ሩቶ አሸናፊነትን በይፋ ያፀናው ።የጠቅላይ ፍ/ቤት ዋና ሀላፊ ማርታ ኩም ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው መጭበርበሩን የሚያረጋግጡ አሳማኝ ማስረጃዎች ራይላ ኦዲንጋ አልቀረቡም ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል::

#ጀርመን

ጀርመን በነዳጅ ዘይት ምርቶች ዋጋ መናር የተጎዱ ዜጐችን ይደግፋል ያለችውን የ65 ቢሊየን ዩሮ የድጐማ ድጋፍ ይፋ አደረገች ::በተለይ በመጪው የክረምት ወራት ሊከሠት የሚችለውን የነዳጅ ዋጋ ንረት ለመቋቋም ነው ሲሉ የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ተናግረዋል።ጀርመን ከዚህ ቀደም ካፀደቀቻቸው ድጋፎች የአሁኑ በእጥፍ የሚበልጥ እና በተለይ በነዳጅ ዋጋ ንረት ለተጓዱ የአገሪቱ ዜጐች ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

#ጋና

የጁሚያ ኩባንያ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው ሸቀጦችን በሰው አልባ አውሮፕላን የማከፋፈል ስራውን በጋና አስጀምሯል ::የጅሚያ ኩባንያ እና የዚፕላይን ድርጅት ከ 3 ወራት የሙከራ መርሃ ግብር በኋላ ነው በመላ ጋና ሸቀጦችን በሰው አልባ አውሮፕላን የማድረስ ስራቸውን በይፋ ማስጀመራቸው የተገለፀው።የሰው አልባ አውሮፕላኖቻችን በየእለቱ በሚያደርጉት 1 መቶ በረራዎች ልዩ ልዩ ግብአቶችን ለደንበኞቻችን በላቀ ፍጥነት እያደረሱ ነው ሲሉ ጀምያ ኩባንያ መግለፁን ቪኦኤ ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New