አዲስ ነገር – የሰላማዊ ሰልፍ መብት
መንግስት የዜጎችን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት እንዲያከብርና ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ በነበሩ ተማሪዎች ላይ ድብደባና እንግልት የፈጸሙ አካላትንም ለህግ በማቅረብ ተጠያቂ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ጠይቋል፡፡
ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ እንዲሁም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚዥንጋ ወረዳ ሴነ ቀበሌ ውስጥ በአሸባሪነት በተፈረጀው ሸኔ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ድርጊቱን በማውገዝ ሰኔ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፎችን ያደረጉ ቢሆንም ሰልፎቹ የጸጥታ ሀይሎች አስለቃሽ ጭስንና ሀይልን በመጠቀም እንደበተኑትና በሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች በነበሩ ሰልፎች ላይ የተደበደቡ እና የታሰሩ ተማሪዎች እንደሚገኙ ኢሰመጉ ገልጿል፡፡
በዚህም መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ በነበሩ ተማሪዎች ላይ ድብደባና እንግልት የፈጸሙ አካላትን ለህግ በማቅረብ ተጠያቂ እንዲያደርግና በጸጥታ አካላት የሚፈጸሙ ህገ ወጥ ተግባሮችን በአስቸኳይ እንዲያስቆም፣ በዚህ ሰልፍ ምክንያት ታስረው የሚገኙ ሰዎችን የአካል ነጻነታቸውን እንዲያከብር እንዲሁም ተገቢውን ማጣራት በማድረግ አፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጥ ኢሰመጉ ይፋዊ ድረ ገጹ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New