አዲስ ነገር – የስንዴ ምርት ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከሰሃራ በስተደቡብ ካሉ ሃገራት በስንዴ ምርት ቀዳሚ ስፍራ ላይ መሆንዋ ተገለፀ።እንደ ቢዝነስ አፍሪካ ዘገባ ከሆነ የኢትዮጵያ የስንዴ ምርት እ.ኤ.አ በ2021 ከነበረው የአሁኑ የ70 በመቶ እድገት ያለው ሲሆን በ2023 ደግሞ ራሷን ችላ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ምርቷን መላክ የሚያስችላት ሁኔታ ላይ ትገኛለች ተብልዋል።ላለፉት አመታት ከባድ ሁኔታዎችን ብታስተናግድም አስደናቂ ለውጥ ያሳየች መሆኗና በምግብም ራሷን ለመቻል እየሰራች እንደሆነ ተገልጿል።በሌላም በኩል የዩክሪን እና ሩሲያ ጦርነት አህጉረ አፍሪካ ከፍተኛ የምግብ ቀውስ ውስጥ እንዳስገባትና በአንጻሩ ኢትዮጵያ አግሮ ቢዝነስ ላይ በማተኮር የስንዴ ምርቷን ለማሳደግ መስራቷ የሚበረታታ ነው ተብሏል።በዚህም አነስተኛ ይዞታ ያላቸውን ገበሬዎች የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ በማገዝ የሃገሪቱን የምግብ ዋስትና ማስጠበቅ እንደሚቻልና ሌሎች ሃገራትም ከኢትዮጵያ ትምህርት ሊወስዱ እንደሚገባ አመላክቷል።
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New