አዲስ ነገር – የተያዙት የነዳጅ ቦቴዎች
ነዳጅ ጭነው በየመንገዱ ተደብቀው የነበሩ 15 የነዳጅ ተሽከርካሪዎች በአፋር ክልል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘግቧል፡፡
ጋላፊ ከተባለው ቦታ አንስቶ ሳርዶ ተብሎ እስከሚጠራው አካባቢ ተደብቀው ነበር የተባሉት እነዚህ 15 ነዳጅ የጫኑ ተሸከርካሪዎች በቁጥጥር ላይ የዋሉት በአካባቢው በተደረገ ኦፕሬሽን ስለመሆኑም ተነግሯል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቲ ጫካ ውስጥ ነዳጅ በመቅዳት ላይ እያለ በቁጥጥር ስር ስለመዋሉ የተነገረ ሲሆን ኦፕሬሽኑ ከተጀመረ በኃላ በየስፍራው ተደብቀው የነበሩ ነዳጅ የጫኑ ተሸከርካሪዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል ተብሏል፡፡
በክልሉ ለ3 ቀናት በነዳጅ እጥረት ምክንያት ማደያዎች ለ3 ቀናት ዝግ ሆነው እንደነበር የጠቆመው የአፋር መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ከእርምጃው በኃላ ማደያዎቹ ስራ መጀመራቸውን ዘግቧል፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New