የአሜሪካን ኤምባሲ በኢትዮጵያ የቪዛ አገልግሎት ዳግም ማስጀምሩን ገለጸ
አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ዲቪ ሎተሪን ጨምሮ ሁሉንም አይነት የቪዛ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ኤምባሲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ዛሬ እንዳሰፈረው በኮሮና ወረርሽኝና በኢትዮጵያ ተጥሎ በነበረው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት አቋርጦት የነበረውን አገልግሎት መልሶ ማስጀመሩን ገልጿል፡፡
የቪዛ ጥያቄ ያስገቡ ዜጎች ለረዥም ጊዜ የተከማቸ ጥያቄ በመኖሩ በትዕግስ አንዲጠብቁ ኤምባሲው ያሳሰበ ሲሆን የቪዛ ቃለምልልሶች የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ባወጣው የቅድሚያ አገልግሎት መስፈርት መሰረት የሚከናወን መሆኑን አምልክቷል፡፡
የኤምባሲው ሰራተኞች በርካታ የቃለመጠይቅ ቀጠሮዎች አንዲሰጡ ጥረት እደረጉ መሆኑን የገለጸው ኤምባሲው አገልግሎት ፈላጊዎች ለቃለመጠይቅ ሲመጡ አስፈላጊውን ሰነዶች በመያዝ ለአገልግሎቱ መቀላጠፍ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላላፏል፡፡