125ኛውን የአድዋ ድል በዓል በሁሉም ክልሎች እንዲከበር ሲሰራ የቆየው ስራ ስኬታማ ነበር-የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር

125ኛው የአድዋ ድል በዓል አከባበርን በሁሉም ክልሎች በክልል ደረጃ እንዲከበር ሲሰራ የቆየው ስራ ስኬታማ እንደነበር የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚንስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው አብዛኞቹ ክልሎች እስከ ወረዳ ድረስ ማህበረሰቡ አድዋን እንዲረዳ እና ከአድዋ ልንወስዳቸው የሚገቡ ትምህርቶችን መነሻ አድርጎ ማክበር ችሏል ብለዋል።

ሚኒስትሯ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚኖሩ የማጠቃለያ መርሐ ግብሮችን ዝርዝር የገለፁ ሲሆን በመርሃ ግብሩም ከየካቲት 19 እስከ የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም የስዕልና ቅርጻ ቅርጽ አውደ ርዕይ፣ የፎቶና መጽሃፍት አውደ ርዕይ፣ የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም ሚኒስትሯ በዓሉን የሚገልጽ ቴአትር፣ የአድዋ ታሪክ በምሁራን እይታ የሚል የፓናል ውይይት፣ በብሔራዊ ሙዚየም፣ በብሔራዊ ቴአትር፣ በኩባ ወዳጅነት ፓርክ፣ በአንድነትና በወዳጅነት ፓርክ እንደሚከበር ገልፀዋል።