Others

የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ ፕራይዝወርዝ ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማን ዘጠነኛ የግብይት አባሉ አድርጎ መቀበሉን ይፋ አደረገ።

ባንኩ በኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደ ሥነ – ሥርአት የአባልነት የምስክር ወረቀቱን ተረክቧል።

ይህ አባልነት የገበያውን የግብይት አባላት ቁጥር ወደ ዘጠኝ ከፍ ያደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ እያሳየ ያለውን እድገት የሚያመለክት ጉልህ ምዕራፍ ነው ተብሏል።

ባንኩ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፈቃድ በማግኘት እና የገበያውን የአባልነት መስፈርቶች በሙሉ በማሟላት የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች የግብይት አባልነቱን አረጋግጧል።

ፕራይዝ ወርዝ ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ በገበያው የግብይት ስርአት አማካኝነት ደንበኞቹን ወክሎ የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ግብይቶችን ማከናወን እንደሚችል ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዮዲት ካሳ ከፕራይዝወርዝ ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ ጋር እንሰራለን ብለዋል።