EBS SPORT – የ5 ተጫዋቾች ከብሄራዊ ቡድኑ መቀነስ እና ሌሎችም መረጃዎች

  • 5 ተጫዋቾች ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተቀንሰዋል፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ 28 ተጫዋቾች ተመርጠው ዝግጅታቸውን በባንክ ሜዳ ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን ከሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች መልስም የመጨረሻ 23 ተጫዋቾች ተለይተዋል ፡ በዚህም ቢኒያም በላይ እና  ሰይድ ሀብታሙን ጨምሮ 5 ተጫዋቾች ከቡድኑ ውጪ ሆነዋል፡፡
  • ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአቋም መፈተሸ ጨዋታውን ከሌሴቶ አቻው ጋር አድርጎ 1-1 ተለያይቷል፡፡ ለዋልያዎቹ ዳዋ ሁጤሳ ሲያስቆጥር የሌሴቶዎቹን የአቻነት ግብ ደግሞ ጃኒ ሳባሲቶ ከመረብ ጋር አዋህዷል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ በማጣሪያው ከማላዊ እና ግብፅ ጋር የሚጫወት ሲሆን የፊታችን አርብ ወደ ሊልዮንጎ የሚያቀኑ ይሆናል፡፡
  • 5ኛው የሴካፋ የሴቶች የእግር ኳስ ሻምፒዮና የፊታችን ረቡዕ በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ጅማሮውን ሲያደርግ ኢትዮጵያ የምድቡን የመጀመሪያ ጨዋታ ከዛንዚባር አቻዋ  ጋር ታደርጋለች፡፡ ለ3ኛ ጊዚ በሻምፒዮናው የሚሳተፉት ሉሲዎቹ ወደ ኒጂሩ ዛሬ ረፋድ የተጓዙ ሲሆን በመጪው ሃሙስ በ7 ሰዓት ከዛንዚባር ጋር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
  • የሰዎች ለሰዎች የበጎ አድራጎት ማህበር መስራቹን ካርል ሄንዝ  ለመዘከር  የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ሊዘጋጅ ነው፡፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በጎ ምግባሮችን በመከወን አንቱታን ያተረፉትን ጀርመናዊ ለማስታወስ የስፖርት ልዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ ሲሆን በመጪው ሰኔ 19 ደግሞ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የጎዳና ላይ ሩጫ ይካሄዳል፡፡
  • ሆላንዳዊን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንግ ሃግን የቀጠረው ማንችስተር ዩናይትድ በክረምቱ የዝውውር ወቅት እስከ 4 የሚደርሱ ተጫዋችን ሊያዛወር እንደሚችል ተገልፅዋል፡፡ ከ150 ሚሊየን ፓውንድ በላይ ለዝውውር የመደበው ክለቡ ፍራንኪ ዲዮንግ ዳርዊን ኑኔዝ ክርስቶፎር ንኩኩ እና ንጎሎ ካንቴ የክረምቱ ዝውውር ዋነኛ እቅዶቹ ናቸው፡፡
  • የቪኒሺየስ ጁኒየር ፡ ኤደር ሚሊታኦ እንዲሁም የሉካ ሞድሪችን ውል ለማራዘም ከተጫዋቾቹ ጋር የተስማማው ሪያል ማድሪድ የፈረንሳዊውን የሞናኮ አማካይ ኦውሪየን ቱቾሜኒን ዝውውር ለማገባደድከ ሞናኮ  ጋር የመጨረሻውን ድርድር እያደረገ መሆኑም ተገልፅዋል፡፡ ክለቡ ለዝውውሩ እስከ 80 ሚሊየን ፓውንድ ፈሰስ እንደሚያደርግም ተሰምቷል፡፡ 
  • በመጪው አመት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ቦታቸውን ከአርሰናል የወሰዱት ቶትንሃም ሆትስፐርሶች ቀድመው ወደ ዝውውር መስኮቱ የገቡ ሲሆን ክሮሺያዊውን ኢቫን ፔርሲችን ከኢንተር ሚላን አዛውረዋል፡፡ የመስመር አማካዩ ለሰሜን ለንደኑ ክለብ የሁለት አመት ኮንትራት ለመፈረም ተስማምቷል፡፡
  • ባሳለፍነው ክረምት ከባርሴሎና ጋር እለያያለው ብሎ እንዳልገመተ ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ገለፀ፡፡ በክረምት የዝውውር መስኮት ምን ተፈጥሮ እንደነበር ለመረዳት እቸገራለው በወቅቱ ባርሴሎናን ለቅቄ እሄዳለው ብዮ አልጠበቅኩም ነበር ያለው ሚሴ በመጪው አመትም በፓርክ ደፕሪንስ እንደሚቆይም ፍንጭ ሰጥቷል፡፡
  • የሞሮኮ ክለብ ዊዳድ ካዛ ብላንካ የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ሰኞ ምሽት በስታድ መሃመድ 5ኛ በተደረገው እና በርካታ ታዳሚያን በስቴዲየም ተገኝተው ባደመቁት ጨዋታ የሞሮኮው ክለብ ዊዳድ ዙሃሪ አል ሙታራጂ ባስቆጠራቸው ገቦች አል አህሊን 2-0 በማሸነፍ የአህጉሪቱን የክለቦች ዋንጫ ለ3ኛ ጊዜ ማሸነፍ ችሏል፡፡ የድለላ ስራ ነው የምትሰራው ታውቆባታል ፡፡
  • የአውሮፓ ሀገራት ሊግ እና የአለም ዋንጫ የማጣሪያ ወሳኝ ፍልምያዎች ረቡዕ ምሽት ይደረጋሉ፡፡ በምድብ 4 ያሉትን ፖላንድ እና ዌልስን የሚያገናኘው የኔሽን ሊጉ ጨዋታ በስታዲዮ ማጀስኪ ፖላንድ እና ዌልስን ምሽት 1 ሰዓት ያገናኛል፡፡ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ በሀምደን ፓርክ ስኮትላንድ እና ዩክሬን ምሽት 3፡45 የጥሎ ማለፍ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New