EBS SPORT- ፈረንሳይ እንግሊዝን 2ለ1 በማሸነፍ የግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀለች
ፈረንሳይ እንግሊዝን 2ለ1 በማሸነፍ የግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለች የመጨረሻዋ ሀገር ሆናለች። ሰማያዊዎቹን ባለድል ያደረጉትን ግቦች ትችዋሜኒ እና ኦሊቬ ዠሩ በስማቸው ሲያስመዘግቡ ሶስቱ አናብስትን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ሃሪ ኬን በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል። ዠሩ በ53 ግቦች የፈረንሳይ ከፍተኛ አስቆጣሪነቱን አስቀጥሏል። ሃሪ ኬን ለእንግሊዝ ያስቆጠራቸውን ግቦች 53 በማድረስ የሃገሪቱ ከፍተኛ አስቆጣሪነት ክብረወሰንን ከሩኒ ጋር ተጋርቷል። በአራት ግቦች በአለም ዋንጫ ታሪክ በርካታ የፍጹም ቅጣት ምቶችን ያስቆጠረ ተጨዋች የሆነው ይህ ኮኮብ ሃገሩን አቻ ማድረግ የምትችለውን የፍጹም ቅጣት ምት ሳይጠቀምባት ቀርቷል። ፈረንሳይ ከ1998 ብራዚል በኋላ ክብሯን ለማስጠበቅ የምትጫወት ሃገር ሆና የግማሽ ፍፃሜውን በመቀላቀል የመጀመሪያዋ ሀገር ለመሆን ችላለች።ሃገሪቱ በአለም ዋንጫው እየመራች እረፍት በወጣችባቸው 25 ጨዋታዎች አንድም ሽንፈት አልገጠማትም።24ቱን ስታሸንፍ በአንዱ አቻ ወጥታለች።በግማሽ ፍፃሜውም ሞሮኮ ከፈረንሳይ የሚገናኙ ይሆናል።
22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ #ማክሰኞ ታህሳስ 4, 2015 አንድ መርሃ ግብር ይደረጋል። አርጀንቲና ከ ክሮሺያ – 4:00 ምሽት
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New