News

ሩሲያ ትልቁን የአውሮፓ ነዳጅ ማስተላልፍያ ዘጋች!

የአለማችን ዋነኛ የጋዝ አምራች የሆነችው ሩሲያ “ኖርድ ስትሪም ዋን” የተባለውን ዋነኛ ትልቁን የአውሮፓ ነዳጅ ማስተላልፊያ መዝጋቷን አስታውቃለች።
የነዳጅ ቱቦው እደሳ እንደሚያስፈልገው እና 10 ቀናት ይፈጃልም ብላለች። ሩሲያ ምንም እንኳን እደሳ ትበል እንጂ የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ ለጣሉባት ማዕቀብ አጸፋ ምላሽ መሆኑ ይነገራል።
በማእቀቡ ምክንያት ለነዳጅ ማስተላለፊያው በቂ መለዋወጫ አላገኘሁም ስትል በአውሮፓ ህብረት ላይ ጫና ስትፈጥርም ቅይታለች።
ከዚህ ቀደም የሩሲያ ለጀርመን ከሚላከው ነዳጅ ስልሳ ከመቶ ቅነሳ አድርጋ እንደነበርም አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።


የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS