News

አዲስ ነገር – አጫጭር የዓለም ዜናዎች

#ጃፓን

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋሚዬ ኪሺዳ ከሁለት ቀናት በፊት በተካሄደው የ8 ኛው የጃፓን የአፍሪካ ጉባኤ ላይ ነው አገራቸው በአፍሪካ ቀንድ የመጀመሪያውን ልዩ መልዕክተኛ እንደምትሾም ያስታወቁት።ጃፓን ለአፍሪካ የ30 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ ከቀናት በፊት ቃል መግባቷን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

***

#አፍጋኒስታን

የመንግስታቱ ድርጅት በአፍጋኒስታን 6 ሚሊየን ሰዎች ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል አለ።ከዚህም በተጨማሪ በአገሪቱ ከ 30 ሚሊየን የሚበልጥ ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል ብሏል።የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ድጋፎች ማስተባበሪያ ሀላፊ ማርቲን ግሪፊትስ ለጋሽ አገራት በአስቸኳይ የ7 መቶ ሚሊየን ዶላር እርዳታ እንዲሰጡ መማፀናቸውንም አልጀዚራ ዘግቧል።

***

#ሶማሊያ

በሶማሊያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የአሜሪካው የአፍሪካ ወታደራዊ እዝ ዋና አዛዥ ከአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር መምከራቸው ተነግሯል።የአሜሪካው ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል ሚካኤል ላንግሌይ በአሸባሪው አልሸባብ ላይ የሚካሄደውን ዘመቻ አስመልክቶ ነው ከሶማሊያው የመከላከያ ሚኒስትር ጋር በሞቃዲሾ የተወያዩት።በሶማሊያ የአሜሪካ ኤምባሲ ውይይቱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ አሜሪካ ለሶማሊያ አስፈላጊውን የፀጥታ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ቢቢሲ ዘግቧል።

***

#አሜሪካየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለታይዋን ያቀረቡት አዲሱ የጦር መሣሪያ ሽያጭ እቅድ ኮንግረሱ እንዲያፀድቅላቸው ሊጠይቁ መሆኑ ተገለጸ።የባይደን አስተዳደር ለታይዋን የ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር የጦር መሣሪያ ሽያጭ እቅድ ያቀረበው የታይዋን እና የቻይና ፍጥጫ እያየለ ባለበት ጊዜ ነው ::የፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር የጦር መሣሪያ ሽያጭ እቅዱ በአሜሪካው ኮንግረስ እንዲፀድቅ በቅርቡ ሊጠይቅ መሆኑን የዋይት ሀውስ ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ አልጀዚራ ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New