አዲስ ነገር – የመኖሪያ ቤት ኪራይ ደንብ መራዘም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ጫናን ለመቀነስ ላለፈው አንድ አመት በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪና ተከራይን ማስለቀቅ የሚከለክለውን ደንብ ተግባራዊ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የተራዘመውን ደንብ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡና የኪራይ ዋጋ የሚጨምሩ አካላት ካሉ ህብረተሰቡ በ9977 አጭር ቁጥር መጠቆም ይችላል ተብሏል።መረጃውን ያገኘነው ከከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት የማህበራዊ ትስስር ገፅ ነው፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New