News

አዲስ ነገር – የተደበቁት ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች

ከጂቡቲ ተነስተው አዲስ አበባና የተለያዩ ዋና ከተሞች መድረስ የነበረባቸው 200 ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በየሠፈሩ ተደብቀው መገኘታቸውን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰሃረላ አብዱላሂ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት በተለይ አዲስ አበባና ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች ላይ ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን የጠቀሱ ሲሆን ይህም በህገወጥ መንገድ የነዳጅ ቦቴዎቹ በየመንደሩ ተደብቀው የኢኮኖሚ አሻጥር በፈጠሩ የነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን አመልክተዋል።

ዳይሬክተሯ በአፋር፣ መተሃራ፣ በሞጆ፣ በአዳማና በተለያዩ ከተሞች ተደብቀው የተገኙት ቦቴዎች ዛሬ እስከ 10 ሰዓት ድረስ ነዳጁን ወደ ማደያዎች ማድረስ እንዳለባቸው ለባለቤቶቹ ማሳሰቢያ መሰጠቱን የገለጹ ሲሆን በተጨማሪም 10 ሰዓት ተኩል ላይ ነዳጁን ማራገፋቸውን ሪፖርት ካላደረጉ እርምጃ እንደሚወሰድ በመጠቆም ይህንን ቁጥጥር የሚመራ ግብረሃይል መቋቋሙን አስታውቀዋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New