News

አዲስ ነገር – የኢትዮ ቴሌኮም አዲስ መላ::

ቴሌ ብር የሲኔት ሶፍትዌርን ከሚጠቀሙ ከ4ሺህ በላይ ተቋማት ጋር ሊተሳሰር ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮምና ሲኔት ሶፍትዌር ቴክኖሎጂ ቴሌ ብርንና ሲኔት መተግበሪያን ያስተሳሰረ የአገልግሎትና የግብይት ክፍያ መፈፀም የሚቻልበትን አዲስ አሰራር ይፋ አድርገዋል።የሲኔት ሶፍትዌር ተጠቃሚ የሆኑ 4ሺ 237 ተቋማት በቴሌ ብር በመጠቀም ክፍያዎችን እንዲፈፅሙ ያስችላል የተባለው ይህ አሰራር በደረሰኞች ላይ የኪው አር ኮዶችን በማተም የሚፈፀም ስለመሆኑ ተነግሯል።በአዲሱ አሰራር መሰረት የሲኔት ሶፍትዌርን በሚጠቀሙና ከቴሌ ብር ጋር በተሳሰሩ ተቋማት የሚስተናገዱ ደንበኞች ክፍያቸውን የሚፈፅሙት ደረሰኞች ላይ የሚታተመውን ኪው አር ኮድ ከስልካቸው ጋር በማናበብ ይሆናል ተብሏል።አገልግሎቱን የሚጠቀሙ ደንበኞች በቅድሚያ ክፍያቸውን በቴሌ ብር መተግበሪያ ከመፈፀም በተጨማሪ በሞባይል ስልካቸው የሚደርሳቸውን አጭር ቁጥር ለክፍያ ባለሙያዎች በመናገር ሂሳባቸውን ማወራረድ እንደሚችሉ ተነግሯል።በሲኔት ሶፍትዌር እየተጠቀሙ ካሉ 4ሺ 237 ተቋማት መካከል አሁን ላይ ከቴሌ ብር ጋር የተሳሰሩት 31 ተቋማት ብቻ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን በ2015 ይህን ቁጥር ወደ 1000 ለማሳደግ እንደሚሰራ ተነግሯል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New