News

አዲስ ነገር – የክትባት ምርምር ማዕከል

አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት በኮሪያ ከሚገኘው ኢንተርናሽናል ቫክሲን ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የክትባት ምርምር ማዕከል በኢትዮጵያ በይፋ ከፍቷል፡፡
ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ክትባት እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር ክትባቶች ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ እንዲሆኑ በማለም እንደተከፈተ የተነገረለት ይህ ማዕከል ክትባትን በማበልፀግ እና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ከሚገኘው መረጃ እና እገዛ በዘላቂነት በክትባት ዙሪያ ለመስራት ያስችላልም ተብሏል፡፡
አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት እና ኢንተርናሽናል ቫክሲን ኢንስቲትዩት ላለፉት በርካታ አመታት በሽታን በመከላከል ላይ በተለይ በታይፎይድ፣ በኮሌራ እንዲሁም በሌሎች በሽታዎች አብረው ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡
በሌላ በኩል በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የሚመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በ75 ኛው የአለም ጤና ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ መሆኑ የተነገረ ሲሆን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ በአካል የመጀመሪያው በመሆን ግንቦት 14 ቀን 2014 ዓ.ም በጄኔቫ ስዊዘርላንድ በይፋ ተጀምሯል።
“ሰላም ለጤና፥ ጤና ለሰላም!” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለውና ለአንድ ሳምንት የሚቆየው ጉባኤው ስለ አለማችን የማህበረሰብ ጤና አሁናዊና ቀጣይ ስትራቴጅክ ጉዳዮች ቀርበውበት ምክክርና ውይይት እንደሚደረግበት የጤና ሚኒስቴር በማህበራዊ የትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New