Sports

ኢትዮጵያ ሜዳሊያ የምትጠብቅበት የ 1,500 ሜትር ሴትች የፍጻሜ ውድድር

ኢትዮጵያ ሜዳሊያ የምትጠብቅበት የ 1,500 ሜትር ሴትች የፍጻሜ ውድድር ስለ አትሌቶቹ ጥቂት መረጃ:-

#ጉዳፍ ጸጋዬ ገና በ 17 አመቷ በ 2014 በአለም የታዳጊዎች ሻምፒዮና ሀገሯን ወክላ በመሳተፍ በ 1,500 ሜትር የብር ሜዳሊያን ማጥለቅ የቻለችው ጉዳፍ ጸጋዬ በ2019 የዶሃ አትሌቲክስ ሻምፒዮናም የነሃስ ሜዳሊያ ማሸነፏ ይታወሳል፡፡ በዚሁ ርቀት በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በዘንድሮው የውድድር አመት በቤልጊሬድ የወርቅ ሜዳሊያን የግሏ ማድረግ የቻለችው አትሌቷ የማጣርያውን ውድድር በብቃት በመጨረስ ለፍጻሜው ውድድር መድረስ ችላለች አትሌቷ ከአጭር ርቀት በተጨማሪም በረዥም ርቀት በ 5,000 ሜትር በቶኪዮ ኦሎምፒክ የነሃስ ሜዳሊያን ማሳካቷ ይታወሳል፡፡

#ፍሬወይኒ ሃይሉ በፊንላንድ ቴምፐር በተካሄደው የአለም የታዳጊዎች ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም ዓቀፍ መድረክ እራሷን ማስተዋወቅ የቻለችው አትሌቷ በቶኪዮ ኦሎምፒክም በ 1,500 ሜትር ኢትዮጵያን ወክላ በመሳተፍ 4ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች፡፡ በሰርቢያ ቤልግሬድ የአለም የቤት ውስጥ ውድድር በ 800 ሜትር ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ በርቀቱ በቤት ውስጥ ውድድር ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያን ማስገኘት የቻለች የመጀመሪያዋ እንስትም ለመሆን በቅታለች፡፡

#ሂሩት መሸሻ በ2019 በሞሮኮ ራባት በተደረገው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ በ 800 ሜትር ውድድር የወርቅ ሜዳሊያን ያጠለቀችው አትሌቷ በቤልግሬዱ የቤት ውስጥ አለም ሻምፒዮናም በ 1,500 ሜትር ውድድር ጉዳፍ ጸጋዬና አክሱማዊት እምባዬን ተከትላ 3ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላ ነበር፡፡በተደጋጋሚ በ 800 ሜትር ውድድር ጥሩ የሚባል ውጤት ማስመዝገብ የቻለችው ሂሩት በ 1,500 ሜትር ማጣርያ ብቃቷን በማሳየት ለመጨረሻው ዙር ውድድር ማለፍም ችላለች፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS