LatestNewsTechnology

ኢትዮጵያ ድሮኖችን በአገር ውስጥ ማምረት ልትጀምር መሆኑን አስታወቀች።

የኢትጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖኖሊጂ ኢንስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ የድሮን ቴክኖሎጂ ላይ ለመስራት ድሮኖችን ለማምረት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብሏል፡፡የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር የሽሩን አለማየሁ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ አገሪቱ በራሷ አቅም ድሮኖችን ማምረት የሚያስችል ስራዎች ተጀምረዋል ነዉ ያሉት፡፡ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ወደ ስራ ለመግባት ስምምነት ላይ መደረሱም ተነግሯል፡፡አሁን ላይ ኢትዮጵያ የምትጠቀማቸዉ ድሮኖች ከዉጭ በማስገባት እንደሆነ የተናገሩት ዶክተር የሽሩን ከቅርብ ጊዜ በኋላ ግን አገር ዉስጥ ይመረታሉ ብለዋል፡፡ኢትዮጵያ በተላያዩ ዘርፎች ላይ የምትጠቀማቸዉ ድርኖች በተበታተነ መልኩ የሚገኙ ከመሆናቸዉ ባለፈ በከፍተኛ ዉጪ የተገዙ ናቸዉ፡፡የድሮን ቴክኖሎጂ በአገር ዉስጥ ተግባራዊ መደረጉም ወጪን ከመቆጠቡ በተጨማሪ ዘርፉን ያሳድገዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡በኢትጵዮጵያ የድሮን ቴክኖሎጂ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ያስረዱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በተለይም በግብርናዉ እና በጤናዉ ዘርፍ የሚታዩ የተደራሽነት ችግሮችን ለመፍታት ይረዳል ተብሏል፡፡