Technology

ማይክሮሶፍት ለዊንዶውስ ተጠቃሚዎች ወርሃዊ የደህንነት ማዘመኛ ለቀቀ::

ማይክሮሶፍት በወርሃዊ የደህንነት ዝመናው ለዊንዶውስ ተጠቃሚዎች 83 የጥቃት ተጋላጭነቶችን የሚደፍን የደህንነት ማዘመኛ መልቀቁን አስውቋል፡፡የደህንነት ማዘመኛዎች መካከል ድንገተኛ ለሆኑ የጥቃት ተጋላጭነቶች የሚውሉ የከፍተት መሙያዎች ይገኙበታል፡፡ዛሬ የተለቀቀው የደህንነት ዝመና የፈረንጆቹ 2021 ከገባ ወዲህ የመጀመሪያው ሲሆን በአጠቃላይ 83 ክፍተቶችን እንደሚደፍን ተገልጿል፡፡እነዚህ ማዘመኛዎች ለዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም፣ ለኤጅ የመረጃ ማፈላለጊያ (ብሮውዝርስ)፣ ለማይክሮሶፍት ኦፊስ ለኦዲዮ ቪዥዋል፣ ለአጥፊ ሶፍትዌር መከላከያ ኢንጂኖች)፣ ለማይክሮሶፍት የመረጃ ቋት አስተዳደር ስርዓት እና ለሌሎች ክፍተቶች የሚውሉ ናቸው፡፡በጥር ወር የደህንነት ማዘመኛ ከቀረበላቸው መካከልም የመረጃ መንታፊዎች በርቀት ሆነው የተጠቃሚዎችን መረጃ መጥለፍ የሚያስችላቸው የደህንነት ክፍተት አደገኛው ክፍተት መሆኑን የኢቫንቲ የደህንነት ምርቶች ዳይሬክተር ክሪስ ጎትል ጠቁመዋል፡፡በመሆኑም የዊንዶውስ ተጠቃሚ ተቋማት እና ግለሰቦች የሚጠቀሙት ማይክሮሶፍት የማልዌር መከላከያ ኢንጂን ስሪት (version 1.1.17700.4) ወይም ከዚያ በላይ መሆኑን እንዲያረጋግጡ ኃላፊው መክረዋል፡፡በመሆኑም የማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ተጠቃሚዎች በዛሬው እለት የተለቀቀውን የደህንነት ማዘመኛ በመተግበር በስርዓተ ኮምፒውተሩ እና በመረጃዎች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ጉዳቶችን እና ስርቆቶችን እንዲከላከሉ መመከሩን ኢመደኤ ዘግቧል።