አዲስ ነገር – ህገወጦችን መለየት

ከሳውዲ አረቢያ ተመላሽ ዜጎች መካከል አሉ የተባሉ አጥፊዎችን በምርመራ ለመለየት የሚያስችል የምርመራ ቡድን ወደ ሥራ ሊገባ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
መንግሥት በሰዎች የመነገድ ወንጀልና በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን ከመውሰድ ባሻገር ወንጀሉን ለመግታት የሚያስችል የሕግ ሥርዓት የተዘረጋ ቢሆንም እስካሁን የሚጠበቀውን ያህል ውጤት ማምጣት አለመቻሉ ተገልጿል።

ታድያ መሰል ወንጀሎችን የሚፈጽሙ አካላትን ለመለየትና ለህግ ለማቅረብ ልዩ የምርመራ ዕቅድ በማዘጋጀት የምርመራ ቡድን ወደ ስራ እንዲገባ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ከፍትህ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ተመልክተናል፡፡

በተጨማሪም ሕገ-ወጥ ድርጊቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥር እየሰደደ በመምጣቱ ዜጎችን ለአስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና እንግልት በመዳረጉ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣና የወንጀሉ ተጠቂ ቤተሰቦች ወይም ማህበረሰቡ አዘዋዋሪዎችን ለህግ አስከባሪ አካላት እንዲጠቁሙም ጥሪ ቀርቧል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:00 ሰዓት እስከ 7:30 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መረጃዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New