News

አዲስ ነገር – በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የዓይን ሞራ ግርዶች ቀዶ ህክምና በነጻ ሊሰጥ መሆኑን ተገለጸ፡፡

በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ኮሌጅ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል የዓይን ሞራ ግርዶች ቀዶ ህክምና በነጻ ሊሰጥ መሆኑን ሆስፒታሉ አስታወቀ፡፡

የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍሉ ኤች ሲ ፒ በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት እገዛ 500 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ከሰኔ 6 እስከ 12/2014 ዓ.ም እንደሚያደርግ ያስታወቀ ሲሆን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ፈላጊ
ዜጎች የነጻ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ሆስፒታሉ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መረጃ ገልጿል፡፡

ታዲያ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ቅድመ ምርመራ፣ ልየታና ምዝገባ ስለሚያስፈልግ በግንቦት ወር ባሉት ቅዳሜና እሁድ ቀናቶች ማለትም ግንቦት 6 እስከ 28 ድረስ በኮሌጁ የስልክ አገልግሎት 967 በመደወል ለቅድመ ምርመራ፣ ልየታና ምዝገባ ቀጠሮ መያዝ አስፈላጊ መሆኑንም ሆስፒታሉ እወቁልኝ ብሏል፡፡
የዓይን ሞራ ግርዶሽ የዐይን ብሌን በዳመናማ መሰል ነገር እየተጋረደ መምጣት ሲሆን በጊዜ ህክምና ካላገኘ በሂደት ዕይታን ሊያሳጣ የሚችል በአብዛኛው በእድሜ መግፋት ብሎም በኑሮ ዘይቤ ሳቢያና በዘር ሊተላልፍ የሚችል የዐይን በሽታ ነው፡፡