ለተሠንበት ግደይ ወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች

በአሜሪካ የደመቀችው ለተሰንበት ግደይሕልሜ እውን ሆነ፣ ይህ ድል ለእኔ ከዓለም ክብረወሰን የበለጠ አስፈላጊ ነው አሁን ህልሜ 5,000 ሜትርን በማሸነፍ 2 የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማሳካት ነው በእግዚአብሔር እርዳታ እንደማሳካው እርግጠኛ ነኝ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ከድሉ በኋላ የተናገረችው ቃል ነው::የ5,000 ሜትርና የ 10,000 ሜትር  የአለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነችው ለተሰንበት ግደይ በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው የኦሎምፒክ መድረክ  ለሀገሯ የነሀስ ሜዳሊያዎችን ማሳካቷ ይታወሳል። አትሌቷ ከ 3 አመት በፊት በ ኳታር ዶሃ በተካሄደው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ድንቅ ፉክክር አድርጋ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።በዘንድሮው የአለም  አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች መካከል አንዷ የነበረችው  ስመ ጥሯ ለተሰንበት  ከነ ሄለን ኦብሪና ሲፈን ሃሰን ከፍተኛ ፉክክር ቢገጥማትም እልህ አስጨራሽ ትግል በማድረግ ወርቁን በእጇ አስገብታለች።አትሌቷ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ፊቷን ወደ ግማሽ ማራቶንና ወደ ማራቶን ማዞሯ ይታወቃል።እንኳን ደስ አለሽ ሃገራችን!!!!!!!!!!!