News

በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጪ ሃገር ዜጎች

በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጪ ሃገር ዜጎች እና የውጭ ሃገር ዜጋን ያከራዩ እንዲያስመዘግቡ ተጠየቀ
የመኖሪያ ፈቃዳቸው ወይም የሚቆዩበት ጊዜ ያለፈበት፣ምንም አይነት ቪዛም ሆነ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው፣ በስደተኝነት ፈቃድም ያለፈቃድም በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ዜጎች ምዝገባ እንዲያደርጉ የተጠየቀው ለ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሲሆን ቀነ ገደቡም ከሀምሌ 11 እስከ 25 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ምዝገባ መሆኑ ተመልክትዋል፡፡
የምዝገባ ቦታዎች: በአዲስ አበባ በሁሉም ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጽ/ቤቶች እና ፒያሳ በሚገኘው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሲሆን የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች እንዲሁም በቢሾፍቱ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጽ/ቤቶች መሆኑ ተነግሯል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS