ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሪፖርተርነትና በዜና አንባቢነት ለተወዳደራችሁ !

ለአጭር ጊዜ ባወጣነው የስራ ማስታወቂያ ወደ 1000 አመልካቾች ከኢቢኤስ ጋር ለመስራት ፍላጎት ማሳየታችሁን ተመልክተናል። የኢቢኤስ ቴሌቭዥን ላሳያችሁት ፍላጎትና ጥረት ለመላው አመልካቾች እያመሰገንን የዜናና ወቅታዊ ፕሮግራሞች ዋና ክፍል ባወጣው መስፈርት መሰረት የመጀመሪያ ዙር ያለፋችሁ 80 አመልካቾች የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 30 ቀን 2014ዓ.ም በኢሜል በምናሳውቃችሁ ሥፍራ እንድትገኙና የሙያ ግንዛቤ የጽሑፍና የክህሎት ፈተና እንድትወስዱ እናሳስባለን።
እጩ ተወዳዳሪዎች ለማመልከቻ በተጠቀማችሁበት ኢሜል በሚቀጥሉት ሰዓታት በኢሜል የምንልክላችሁ መሆኑን እናሳውቃለን ::

ኢቢኤስ ቴሌቪዥን የእርሶና የቤተስብዎ ቀዳሚ ምርጫ !