ለ55 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል

በተያዘው የ2014 በጀት ዓመት ሩብ ዓመት በአዲስ አበባ ለ55 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን የከተማዋ የስራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት አስታወቀ፡ በቀጣይም ለ350 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታስቦ እየተሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመዲናዋ የስራ ዕድል ፈጠራ ም/ቤትን የ2014 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ትላንት ገም ግመዋል ኢትዮጵያ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር በከተማዋ የተፈጠረው የስራ እድል አበረታች ነው ቢባልም ከጦርነቱ ማብቃት በኋላ ሊከተሉ የሚችሉ ጥያቄዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ ሊሰራ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ ዘገባው የሪፖረትራችን ማዕዶት አየለ ነው፡፡ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።Telegram: https://t.me/ebstvworldwideFollow us on: https://linktr.ee/ebstelevision#ኢቢኤስ#EBS