EthiopiaNews

ሌጲስ መንደር

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 54 ምርጥ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ውስጥ የኢትዮጵያው ሌጲስ መንደር አንዱ ነው አለ ።

ሲኤን ኤን በ2023 በአለም ዙሪያ የሚገኙና በተፈጥሮ መልከአምድራቸው፤ ሰው ሰራሽ ገጽታቸውና በሚሰጡት አገልግሎት ጭምር በጎብኝዎች ተመራጭ ከሆኑ ቦታዎች መካከል የኢትዮጵያው ሌጲስ መንደር አንዱ ነው ብሏል፡፡
ሌጲስ  የሚገኘው ከአዲስ አበባ 160 ኪሎሜትር በኦሮሚያ ክልል አርሲ ነገሌ አካባቢ ሲሆን፤ አካባቢው በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ የአእዋፍ ዝርያዎችና የተለያዩ የዱር አራዊት መገኛ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ቦታው ከተፈጥሯዊ ገጽታው ጎን ለጎን  የአካባቢው ማህበረሰብን የሚወክሉና በተለያየ አሰራር የሚቀርቡ የእጅ ስራ ውጤቶች ሌላው በቱሪስቶች ተመራጭ የሚያደርገው መሆኑን ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የጮቄ ተራራ በፈረንጆቹ 2021 ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም ምርጥ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራ ውስጥ ሲካተት በ2022 ደግሞ ወንጪ ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ይታወሳል፡፡