ልዩ ምርጫ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ በ442 ወታደራዊ ካምፖች እና በ82 መጠለያ ጣቢያዎች ለመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ትናንት ድምጽ መስጠታቸውን ገለጸ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ በትናንትናው እለት በወታደራዊ ካምፖች እና መጠለያ ጣቢያዎች የተካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሀን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ቦርዱ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በመደበኛው ጠቅላላ ምርጫ በልዩ ሁኔታ ላልተሳተፉ ዜጎች የድምጽ መስጫ ቀን እንደሚያመቻች ገልጸዋል።
ቦርዱ ለዚሁ የሚሆን ልዩ የምርጫ ጣቢያ በማዘጋጀት የተለያዩ ስራዎችን ማከናወኑን የጠቆሙ ሲሆን ለአስፈጻሚዎች እና ለአስተባባሪዎች ስልጠና መስጠቱን ገልጸው፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረጉንም ተናግረዋል።
በካምፖች በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ትናንት ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ድምጻቸውን መስጠታቸውን ገልጸዋል።
ትናንት እንደታቀደው በሁሉም ወታደራዊ ካምፖች እና የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ መጠለያዎች በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ሲካሄድ የቆየው ምርጫ ከአንድ ጣቢያ ውጪ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ገልጸው፤ በድምጽ አሰጣጥ ሂደቱም ያጋጠመ ችግር እንደሌለ ጠቁመዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
