ሕዝበ ውሳኔ በሰሜን ኢትዮጵያ
በሰሜን ኢትዮጵያ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ መንግሥት መወሰኑ ተነገረ
በጉዳዩ ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጽ/ቤት እንዳለው በሰሜን ኢትዮጵያ አከራካሪ በሚባሉ ቦታዎች በህገመንግስቱ መሰረት ህዝበ -ውሳኔ እንዲደረግ አቅጣጫ ማስቀመጡን አስታውቋል፡፡
እነዚህኑ አካባቢዎች በተመለከተ የፌደራል መንግስት ከትግራይና ከአማራ ክልሎች አመራሮች ጋር የጋራ ውይይት ከተደረገ በኋላ በህገመንግስቱ መሰረት መግባባት የተደረሰባቸው አቅጣጫዎች እንዲተገበሩ ይደረጋል ነው የተባለው፡፡
በዚህም መሰረት ከእነዚህ ስፍራዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቄቸው እንዲመለሱና ወደእርሻ ስራቸው እንዲገቡ ከስምምነት ላይ መደረሱ የተነገረ ሲሆን ፤ ከዚያው አካባቢ በተመረጡ ሰዎች እንዲተዳደርና የፀጥታው ስራም ሙሉ በሙሉ ለፌደራል መንግስት እንዲተላለፍ ከመግባባት ላይ መደረሱ ነው የተገለጸው፡፡