EthiopiaNews

መስከረም 1 የሚጀምረው አዲሱ የኤሌክትሪክ ታሪፍ

ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ሽፈራው ተሊላ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ሆኗል።

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ደንበኞቹ በማሻሻያው እንዳይጎዱ ድጎማ መደረጉን የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ድጎማ ከማድረግ በዘለለ በየሩብ አመቱ ተከፋፍሎ ለአራት አመታት የሚተገበር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የታሪፍ ማሻሻያው የመኖሪያ ቤት፣ የንግድ ተቋማት፣ ዝቅተኛ ኢንዱስትሪ፣ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ እንዲሁም የመንገድ መብራት ተጠቃሚ ደንበኞች በሚል መከፋፈሉን አስታውቀዋል።
በዚህም ከ0 እስከ 200 ኪሎ ዋት በሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞች የድጎማው ተጠቃሚ የሚሆኑ ሲሆን ድጎማው የመጨረሻው የትግበራ ዓመት ድረስ ይተገበራል ብለዋል፡፡
በዚህ መሰረት የሚደረገው ድጎማ የሚከተለውን ይመስላል፤
• ከ50 ኪሎ ዋት በሰዓት በታች ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 75 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፣
• ከ50 ኪሎ ዋት በሰዓት እስከ 100 ኪሎ ዋት በሰዓት ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 40 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፣
• ከ200 ኪሎ ዋት በሰዓ እስከ 300 ኪሎ ዋት በሰዓት ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 4 በመቶ ይደጎማሉ፣
• ከ400 ኪሎ ዋት በሰዓት እስከ 500 ኪሎ ዋት በሰዓት የሚጠቀሙ ከሆነ ያለምንም ድጎማ የሚከፍሉ ይሆናል ተብሏል፡፡
እንዲሁም ከ500 ኪሎ ዋት በሰዓት በላይ የሚሆነውን የሚጠቀሙ ደግሞ ሌላውን ተጠቃሚ የሚደግፉበት የጎንዮሽ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ እንደሚደረግ ጠቅሰዋል፡፡