ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ አገልግሎቶችን እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከፊታችን ሚያዝያ 2014 ዓ.ም ጀምሮ የተመረጡ የቴሌኮም አገልግሎቶችን ለመስጠት ሙከራ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡በአሁኑ ጊዜ የድምጽ፣ ጽሁፍና የዳታ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የመረጃ ማዕከል ግንባታ ማከናወኑን የጠቆመው ድርጅቱ በቀጣይ ጊዜያት ሌሎች አገልግሎቶችን ለመጨመር የሚያስችል የግንባታው ቀሪ ስራዎች ይከናወናሉ ብሏል፡፡አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ በ2ጂ፣ 3ጂ እና 4ጂ ቴክኖሎጂ ወደስራ ለመግባት እንደታቀደ የተመለከተ ሲሆን የ5ጂ ቴክኖሎጂን ሙከራ እያደረገ እንደሆነና ከኢትዮ ቴሌኮምም መሰረተ ልማት ለመጋራት እየተደራደረ ስለመሆኑ ሰምተናል፡፡አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ ኮምቦልቻ፣ ሀረር፣ ድሬዳዋ እና ጅግጅጋ አገልግሎቶቹ ከሚጀመርባቸው አካባቢዎች ዋነኞቹ ሲሆኑ የሞባይል ኔትወክር ሳይቶች ተከላ እየተከናወነ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ በ07 የሞባይል መነሻ ኮድ አገልግሎት እንደሚሰጥ የተጠቆመ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ 200 ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል መፍጠር እንደቻለና በ10 ዓመት ውስጥም ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እንደሚሰራ ሲነገር አድምጠናል፡፡ ዜናው የሪፖርተራችን ሃና አብደታ ነው፡፡
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።
Telegram: https://t.me/ebstvworldwide
Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision