EthiopiaNews

ስትራቴጂ የሴቶች ጥቃትን ለመከላከል

በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችና ወንጀሎችን ለመከላከል ተፈፅሞ ሲገኝም ምላሽ ለመስጠትና ለማስቀጣት ከ2016 እስከ 2020 ዓ.ም የሚቆይ ሁለተኛው ስትራቴጂ ተቀርፆ ወደስራ መግባቱ ተገልጿል፡፡

ፍትሕ ሚኒስቴር ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀም ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የተቋቋመውን ብሔራዊ አስተባባሪ አካል ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር ያለመና ከፌዴራል፣ ከከተማ መስተዳደር እና ከክልል ከተወጣጡ  ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ባካሄደበት ወቅት ነው ይህ የተገለጸው

የመጀመሪያው ስትራቴጂ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰራበት የነበረ እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን አሁን ወደስራ የገባው በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀም ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የተቀረፀው ብሔራዊ ስትራቴጂ በአጠቃላይ በቀድሞው ስትራቴጂ ጥንካሬዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን ተነግሯል፡፤ስትራቴጂው በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀም ጥቃትን ለመከላከል እና በፍትሕ ስርዓት ውስጥ የሚያልፉ ህፃናትን መብት ለማስጠበቅ በአዲስ መልክ ለመንቀሳቀስ በርካታ ባለድርሻ አካላትን ያስተባበረ ስለመሆኑም የፍትህ ሚኒሰቴር መረጃ ያሳያል፡፡

#EBS

#EBSTVNEWS

#EBSTVSPORT

#_7696_WN

https://t.me/ebstvnews

www.ebstv.tv