ስግብግብ ነጋዴዎች
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡን ባልተገባ ሕገ ወጥ መንገድ ለመጠቀም በሚፈልጉ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ የሕግ አስፈጻሚ አካላት እርምጃ እንዲወስዱ ኃላፊነት እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡን በተመለከተ ትላንት ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የለውጥ ሥራዎቻችን ሁሉ ስኬት በባለድርሻ አካላት የተባበረ ጥረት ላይ ይመሠረታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አካሄዳችን ደሃ ተኮር ነው ሲሉ በኤክስ ማህበራዊ ገጻቸው አስፈረዋል፡፡