EthiopiaNews

በልዩ ሁኔታ የሚመዘገቡ መራጮች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በልዩ ሁኔታ የሚመዘግባቸውን መራጮች ምዝገባ መጀመሩን አስታወቀ።

ቦርዱ በተለየ ሁኔታ የሚመዘግባቸው መራጮች የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና በካምፕ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን ያካተተ ነው ብሏል።

ቦርዱ በልዩ ሁኔታ የሚመዘገቡ መራጮች ምዝገባ እስከ ሚያዚያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ መሆኑን ገልጿል።

ቦርዱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና በካምፕ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ቦርዱ ባቋቋማቸው ልዩ ምርጫ ጣቢያዎች የሚመዘገቡ መሆኑን ገልፆ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግን ቦርዱ ለተማሪዎች ባዘጋጀው ልዩ የመመዝገቢያ ድረ-ገፅ የሚመዘገቡ ይሆናል ብሏል።

መረጃው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv