EthiopiaNews

በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ኢትዮጵያውያን

በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መብት፣ ክብር እና ጥቅም የማስጠበቅ ስራዎች ላይ ውይይት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በኤዥያ እና በፓስፊክ ክልል ከሚገኙ የቆንስላ ፅህፈት ቤት ኃላፊዎች ጋር በመሆን የዘጠኝ ወራት የዜጎች የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አፈጻጸም ሪፖርትን ገምግመዋል።

በግምገማው በሀገሪቱ የዜጋ-ተኮር ዲፕሎማሲ ማዕቀፍ መሠረት ዜጎች ህጋዊ የስራ ዕድሎችን እንዲያገኙና መብታቸው ተከብሮ እንዲሰሩ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር ያለውን ቅንጅት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ በጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ነው የተባለው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv