በማድሪድ የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

ትላንት ምሽት በስፔን ማድሪድ ከተማ በተካሄደ የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።በሴቶች 3ሺህ ሜትር አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በ8:22:65 አንደኛ በመውጣት የምንጊዜም ሁለተኛ ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ በበላይነት ስታጠናቅቅ፣ ለምለም ኃይሉ በሁለተኛነት ውድድሯን አጠናቃለች።በወንዶች 1500 ሜትር ደግሞ ሰለሞን ባረጋ 3:35:42 በመግባት በአንደኛነት አጠናቋል።በተመሳሳይ በሴቶች 1500 ሜትር ሂሩት መሸሻ 4:09:42 በመግባት በሁለተኛነት አጠናቃለች።በተጨማሪም፣ በሴቶች 800 ሜትር ሀብታም አለሙ የቦታውን ሰዓት ጭምር በማሻሻል 1:58:94 በመግባት በአንደኛነት ማጠናቀቋ የአፍሪካ አትሌቲክስ ዩናይትድ መረጃ ያመለክታል።