EthiopiaNews

በሰው የመነገድ ወንጀል

የፍትህ ሚኒስቴር መነሻቸውን ከአማራና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በማድረግ ዋና መዳረሻቸውን አዲስ አበባ ባደረጉ የሕፃናት ዝውውር ላይ የሚስተዋለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሰው የመነገድ ወንጀልን ለመግታት፣ የተቀናጀ የጋራ አሠራር መዘርጋት የግድ እንደሚል ገልጿል፡፡

ይህ የተገለጸው የሚኒስቴሩ የብሔራዊ የትብብር ጥምረት ጽሕፈት ቤት ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ፣ ከዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅትና ከዓለም አቀፍ የሕፃናት አድን ድርጅት ጋር በመተባበር በሰው መነገድን ለመከላከል ያለመ የምክክር መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በዚሁ ጊዜም በፌዴራል፣ በክልልና በከተማ አስተዳደሮች መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ለተጎጂዎችና ተጋላጭ ሕፃናት ተገቢውን ጥበቃና ምላሽ መስጠት የሚያስችል የጋራ ግንዛቤ ተፈጥሯል ተብሏል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv