InternationalNews

በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎች

በህገወጥ መንገዶች ከሃገር ወጥተው በተለያዩ ሃገሮች የመኖሪያ ሰነድ ሳይኖራቸው ጠልለው ወይም በእስር ላይ ሆነው ያሉ ዜጎችን ወደሃገር የማስመለሱ ጥረት ቀጥልዋል፡፡

ካለፈው ሚያዝያ ጀምሮ ከ70, 800 በላይ በህገወጥ መንገድ ወደ ተለያዩ የአረብ ሃገራት ገብተው በችግርና በእስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገር መመለሳቸው ነው የተነገረው፡፡
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር በትላንትናው እለት በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 313 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለሱን ገልጸዋል፡፡

ከተመላሾቹ መካከል 263ቱ ወንዶች፣ 44ቱ ሴቶች እንዲሁም 6ቱ ጨቅላ ሕጻናት እንደሆኑ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገለጾ ከነዚህም ዉስጥ 24ቱ ተመላሾች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ናቸው ብሏል፡