በሳዑዲ ዓረቢያ ሞት የተፈረደባቸው ኢትዮጵያዊያን
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ የሳዑዲ ዓረቢያ ባለሥልጣናት የሞት ፍርድ ለተፈረደባቸው ኢትዮጵያዊያን ምሕረት እንዲያደርጉ ተማጸነ።
የጳጳሳቱ ጉባኤ ይሄን ያለው በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ያሉበት ወቅታዊ ሁኔታ እንዳሳሰበው ትናንት ባወጣው መግለጫ ነው።
ጉባኤው በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ላይ በተፈረደው የሞት ፍርድ ያለውን ስጋት እና የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፆ የሳኡዲ አረቢያ ባለስልጣናት ለዜጎቹ ርህራሄ እና ምሕረት እንዲያደርጉ ጠይቋል።
ጉባኤው ዜጎች ከአገራቸው የሚወጡት ለአገራቸው ፍቅር በማጣት ሳይሆን የተሻለ የሥራ ዕድል እና የኑሮ ሁኔታ በመፈለግ መኾኑን ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።
መረጃው ከኢትዮጵያ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
