EthiopiaNews

በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣ

በባሕርዳር ከተማ በሰው ሕይወት ማጥፋት ወንጀል ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው ያምራል አለበል አለሙ የተባለው የጸጥታ አባል በመቀሌ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የትግራይ ክልል ፖሊስ አስታወቀ።

ተጠርጣሪው ግድያ ፈጽሞ ከአካባቢው በመሰወር ሲፈለግ መቆየቱን የጠቀሰው የክልሉ ፖሊስ ታድሏል ጌታሰው ሃይሉ ከተባለ ግለሰብ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው የገለጸው፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ ያምራል አለበል አለሙ የተባለው ተጠርጣሪ ግድያ ፈጽሞ ከአካባቢው በመሰወር ሲፈለግ መቆየቱን ጠቅሰው፤ በመቀሌ ከተማ ተሸሽጎ እንደሚገኝ በመረጋገጡ በተደረገ የተቀናጀ ስራ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ስለእንስቷ አሟሟት ያለው ዝርዝር ነገር የለም፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews