InternationalLatestNews

በቱርክ ደቡባዊ ጠረፋማ የባህር ዳርቻዎች ተባብሶ የቀጠለው የሰደድ እሳት

በቱርክ ደቡባዊ ጠረፋማ የባህር ዳርቻዎች ተባብሶ በቀጠለው የሰደድ እሳት አማካኝነት 8 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችና ጎብኝዎች ተፈናቅለዋል፡፡የአደጋ መከላከያ ሰራተኞች ሰደድ እሳቱን በቁጥጥር ስር ቢያውሉም ሙሉ በሙሉ ግን ማጥፋት አለመቻሉን እና የዚህም ምክኒያት በተለይ በባህር ዳርቻዎቹ የተከሰተው አደገኛ ነፋስና ሙቀት የሰደድ እሳት ማጥፋት ስራዎቹን አዳጋች እንዳደረገባቸው ዶቼቬሌ ዘግቧል።በአደጋው ምክንያት ለተለያዩ የጤና እክሎች የተዳረጉ ከ864 በላይ ሰዎች በጤና ተቋማት የህክምና አገልግሎት ያገኙ ሲሆን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንትም በእሳቱ ክፉኛ የተጠቁ የሀገሪቱ ክፍሎች “የአደጋ ቀጠናዎች” ናቸው ሲሉ በይፋ መሰየማቸውም ተሰምቷል፡፡