በአማራ ክልል ከሥራ ገበታቸው የተፈናቀሉ 2 ,167 የመንግሥት ሠራተኞች ወደስራ እንዲመለሱ ተወሰነ።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መሥተዳድር ምክር ቤት በጸጥታ ችግር ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የተፈናቀሉ 2 ሺህ 167 የመንግሥት ሠራተኞችን ወደሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ መወሰኑን ይፋ አደረገ።
የክልላዊ መንግሥቱ የመሥተዳድር ምክር ቤት ውሳኔውን ይፋ ያደረገው በ11ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ ነው።
ወደስራ እንዲመለሱ የተደረጉት የመንግስት ሰራተኞች በፀጥታ ችግር ምክኒያት ከአመታት በፊት የሥራ ቦታቸውን ጥለው የሄዱ እንዲሁም በግጭቱ ከዚህ ቀደም የተሳተፉ እንደነበር የክልሉ መንግስት ገልጿል።
ወደ ስራ እንዲመለሱ ከተወሰነላቸው 2 ሺህ 167 የመንግስት ሰራተኞች ውስጥ 1337ቱ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች ፣738 መምህራን እና 92 የገቢ ተቋማት ሠራተኞች ናቸው ተብሏል።
ምክር ቤቱ በውሳኔው የመንግስት ሰራተኞቹ ከሚመደቡበት ቀን ጀምሮ ደሞዝ የሚያገኙ መኾናቸውን ገልጿል። መረጃው ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
